ቮይኒች ማኑስክሪፕት እ.ኤ.አ. በ1912 አመተ ምህረት ከተገኘ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ የታሪክ የቋንቋ ተመራማሪዎችን እና ክሪፕቶግራፈሮችን ግራ ያጋባ ጥንታዊና እጅግ ሚስጥራዊ ጽሑፍ ነው ።
ይህ ምስጢራዊው ሰነድ በማይታወቅ ቋንቋ ከመፃፉ በተጨማሪ እስከ አሁን ድረስ የትኛውም ዘመናዊ ወይም ታሪካዊ ዘዴ ሊፈታው ባልቻለ እንግዳ የአጻጻፍ ስልት እና ሚስጥራዊ ኮዶች የተሞላ መሆኑን ተከትሎ ላለፉት በርካታ አመታት ሚስጥራዊ ሆኖ መቆየት ችሏል
ላለፉት በርካታ አመታት በቮይኒች መፀሀፍ ዙሪያ የተደረጉ ምርምሮች ስኬታማ እንዳይሆኑ ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ የመፀሀፉ ፀሀፊ ያለመታወቁ ጉዳይ አንደኛውና ዋነኛው ነው
የቮይኒች ማኑስክሪፕት ፀሀፊ አሁንም ድረስ እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የተፃፉ ጥቂት ፅሆፎች የዚህ ሚስጥራዊና አነጋጋሪ መፀሀፍ ደራሲ ሊሆን ስለሚችል አንድ ግለሰብ ጥቆማ መስጠት ችለዋል