አምባሳደር የወርቅ ማዕከል
በግራውንድ አንደኛ እና ሁለተኛ ወለል ላይ የሚገኙ ሰም እና ዝና ባላቸው ከ90 በላይ ስመ ጥር ወርቅ ቤቶች መጥተው ጥራት ያለው ወርቅ ይገበያዮ
#amleset
#ወርቅ
#mehader
#ዶቃፊልም
አርቲስት ማህደር አሰፋ ከቴሌቲቪ ጋር ተፈራረመች፡፡
የዶቃ ፊልም ፕሮዲውሰር የሆነችው አርቲስት ማህደር አሰፋ ከኢግልላዮን ጋር በዛሬው እለት ስምምነት ፈፅማለች፡፡ በዚህ ስምምነትም ዶቃ የተሰኘውን ፊልሟን በቴሌ ቲቪ ፕላትፎርም ውስጥ አስገብታለች፡፡
ቴሌ ቲቪ ሰኔ 2016 ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት ‹‹6 ሰአት ከለሊቱ›› እና ትዝታ የተሰኙ ፊልሞችን በሞባይል መተግበሪያ ውስጥ ማካተቱ ይታወሳል፡፡ ዛሬ በተደረገው ስምምነት መሰረት ዶቃ ፊልምም በዚህ ውስጥ ተካቷል፡፡ ዶቃ ፊልምን በቴሌቲቪ አፕሊኬሽን አማካኝነት መከራየት የሚቻል ሲሆን ዋጋውም 100 ብር ነው፡፡ የአይፎን ስልክ ላላቸው አፕሊኬሽኑ ስለማይሰራ በቴሌብር አማካኝነት ፊልሙን መከራየትና መመልከት እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡
ዶቃ ፊልም የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ፕሮዲውሰሯ አርቲስት ማህደር አሰፋ እንደተናገረችው ፊልሙን በእንግሊዘኛና ሌሎችም ቋንቋዎች የመተርጎም ስራው እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በቀጣይነት ፊልሙን በአለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ የማሳየትና የማወዳደር እቅድ እንዳለም አስረድታለች፡፡