ወደኋላ አላይም (Wedehuala Alayim) Mesfin Mamo

Опубликовано: 06 Сентябрь 2026
на канале: Mesfin Mamo
21,067
749

It's in my heart to encourage you to go forward with the Lord! You're called to walk in liberty if you believe in the One who died for you on the cross - JESUS!

አዝ፦ ወደ ኋላ አላይም ሽንፈቴን አልቆጥርም
የጠላቶቼን ክስ አላስተናግድም
ወደፊት እያየሁ መንገዴን እሄዳለሁ
የቀድሞ ሽንፈቴን ጠላት ፊት ክጃለሁ

ኋላዬን እያየሁ ብዙ በመቆጨት
ያልተሳካልኝን እያሰብኩ በምሬት
መኖር መች ተለየ ጉድጓድ ከመቆፈር
እያለቃቀስኩኝ ራሴኑ ከመቅበር

ከአንደበት ፍሬ የሰው ሆድ ይጠግባል
ልክ እንደሚያወራው እንደዛው ይኖራል
ሞት ከተናገረ ሞት ባሕር ይዋኛል
ሕይወትን ካወራ ሕይወት ደጅ ይደርሳል

ይቅርታ አግኝቻለሁ ጌታዬ ካንተ እጅ
የተቀመጠውን ከምሕረትህ ደጅ
ሽንፈትን ለማውራት አንደበት የለኝም
ከኤልሻዳይ ሌላ ቋንቋ አይገባኝም

Instagram link:   / mesfinmamomusic  
Facebook link:   / jesusmyinheritance  
Website link: https://mesfinmamo.hearnow.com/niges

Music arrangement: Dawit Getachew, CornerStone Recording Studio
Choir arrangement: Ermias Molla
Video production: Mikias Kassahun, Mikas Pictures