“ያለምክንያት” - yalemkniyat Bisrat Melese (Mimi) Ethiopia Gospel Song 2022
የወደድከኝ ልኬት በሌለው ህያው ፍቅር
የዋጀኸኝ ከነገድ ከቋንቋ ከዘር
ጦር ሳትመዝዝ እጅ ነሳሁልህ አንበረከከኝ
ሳትታገል በጸናው ፍቅር አሸነፍከኝ
እምቢተኛ አመጸኛ
ከኃጥያተኞች ዋና በደለኛ
ለነበርኩት ነፍስህን ሰጥተህ
እስከ መስቀል ሞት ፍቅርን አሳየህ
ተቀበልክልኝ ከሰማይ ወርደህ የሞቴን ጽዋ
ለበደሌ ስሬት ደምህ ፈሰሰ ታርደህ ተሰዋህ
ጥልቅ በሆነ በማይበጠስ በፍቅር ገመድ ገመድከኝ
በማይተመን ዋጋ ገዝተኸኝ ምርኮኛ አረከኝ
አዝ፦ አፍቃሪ እውነተኛ
የልብ ጓደኛ ሚስጥረኛ
ሁሉ ነገሬ ሆነህልኛል
ከጽኑ ፍቅርህ ማን ይለየኛል
የተሳብክበት ሚዛን ሚደፋ ከህይወቴ ክፍል
አንዳችም የለም ሰበብ የሚሆን ዋጋ እንድትከፍል
ያለምክንያት ከቃል ባለፈ ፍቅርን በተግባር ገልጠሀል
ለዓለም ሁሉ የመዳን መንገድ ቤዛ ሆነሀል
አዝ፦ አፍቃሪ እውነተኛ
የልብ ጓደኛ ሚስጥረኛ
ሁሉ ነገሬ ሆነህልኛል
ከጽኑ ፍቅርህ ማን ይለየኛል
ሁሌም ትኩስ ማይበርድ
ያለወረት ሚወርድ
ሚዛን የደፋ አፍቃሪ እንከን ማይወጣለት ፈጣሪ