መምህሬ Bisrat Melese (Mimi) Ethiopia Gospel Song 2022

Опубликовано: 11 Июль 2026
на канале: Mikas Pictures
3,360
66

መምህሬ Bisrat Melese (Mimi) Ethiopia Gospel Song 2022

ልከተል ዱካህን
ልጓዝ መንገድህን
አንተን ብቻ መምሰል ራሴን ላስለምደው
አንተን የመምሰል ምስጥር ያለጥርጥር ታላቅ ነው
መምህሬ
የህይወት መምህሬ/2x
በሁሉ ሆነህ ምሳሌ
ፍቴ ተስለሀል ዘውትር
ሳትደበዝዝ በክብር
ከልብህ ለልቤ ቀርበህ መከርከኝ
እውነትን በፍቅር ገልጠህ አስተማርከኝ
እንዴት እንደምኖር በህግህ ስርዓት
እንዴት እንደምጓዝ መንገዴን በጽናት
የህይወትን ዘይቤ ያስተማርከኝ እውነት
ተጽፏል ላይፋቅ አንዴ በልቤ ፅላት
መምህሬ
የህይወት መምህሬ/2x
በሁሉ ሆነህ ምሳሌ
ፍቴ ተስለሀል ዘውትር
ሳትደበዝዝ በክብር
እንዳልወሰድ በትምህርት ንፋስ
በእንግዳ ምክር ቃሉን በምጣረስ
የሰላሙን ወንጌል ይጫሙ እግሮቼ
የእውነትንም ዝናር ልታጠቅ በርትቼ
ተግቼ ልታጠቅ በርትቼ
አነሳለሁ የእምነቴን ጋሻ
እጋደላለሁ እስከመጨረሻ
የመዳንን ራስ ቁር ደፋለሁ
የመንፈስን ሰይፍ እይዛለሁ
/ህያው ቃልህን እይዛለሁ/
እይዛለሁ ህያው ቃልህን
አነሳለሁ የመንፈስ ሰይፌን
እይዛለሁ ህያው ቃልህን
አነሳለሁ የመንፈስ ሰይፌን