COVID-19 Information Amharic (Page 9)

Опубликовано: 14 Июль 2026
на канале: Migration Health Initiative (Old)
2,332
6

በአደገኛ ሁኔታ የመታመም እድልዎ ከፍተኛ ከሆነ ለጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ይደውሉ።

አንዳንድ ሕመም ያለባቸው ሰዎች በኮቪድ-19 በጣም የመታመም ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

ይህ ማለት በሆስፒታል ውስጥ የመተኛት ፣ ጽኑ እንክብካቤ የመፈለግ ፣ ለመተንፈስ የሚረዳ የመተንፈሻ መሳሪያ የመፈለግ ወይም የመሞት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

ይህ እድሜያቸው 65 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ፣ ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው፣ ነፍሰጡር የሆኑ፣ የስኳር በሽታ፣ እንደ የልብ ድካም፣ የደም ቧንቧ በሽታ፣ የካርዲዮሞዮፓቲቲ ወይም የደም ግፊት ዓይነት የልብ ችግሮች፣ እንደ COPD (ወይም ሥር የሰደደ የሳንባ ችግር) ያሉ የሳንባ ችግሮች፣ ከመካከለኛ እስከ ከባድ አስም ፣መካከለኛ የሳንባ በሽታ ፣ ሳይስቲክ ፋይብሮሲስ እና የpulmonary hypertension፣ ሌሎች እንደ ካንሰር፣ ሥር የሰደደ የጉበት በሽታ፣ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ፣ የደም ማነስ በሽታ፣ ኤችአይቪ፣ ወይም የተዳከመ በሽታ የመቋቋም ሥርዓት ያለባቸው ሰዎች። እንዲሁም እንደ ሴሬብራል ፓልሲ ያለ የነርቭ እድገት ችግር ያለባቸው እና እንደ ትራኪኦስቶሚ፣ ጋስትሮስቶሚ ወይም ፖዘቲቭ ፕሬዠር ቬንቲሌሽን ያሉ የህክምና መሳሪያዎችን የሚጠቀሙ ሰዎችን ይመለከታል።

ከነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ አንዳቸውም ካለብዎት እና በኮቪድ-19 ከተያዙ ለጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ይደውሉ። ለማገገም እንዲረዳዎ መድሃኒት ሊሰጡዎት ይችላሉ፣ ነገር ግን መድሃኒቱን ወዲያውኑ መጀመር አስፈላጊ ነው።

በድንገተኛ ሁኔታ ጊዜ። ከእነዚህ ከባድ ምልክቶች መካከል አንዱ ካለብዎ፣ ወዲያውኑ ወደ 9-1-1 በመደወል ወይም ወደ አስቸኳይ እንክብካቤ ማዕከል ወይም የሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል በመሄድ የድንገተኛ ሕክምና እርዳታ ይጠይቁ። ይህም የመተንፈስ ችግር፣ የማያቋርጥ የደረት ሕመም ወይም ጫና፣ ግራ መጋባት፣ ከእንቅልፍ መንቃት ወይም ነቅቶ መቆየት ያለመቻል ወይም የቆዳ ቀለም ለውጦችን ያካትታል።