በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የጤና እንክብካቤ ማግኘት ይችላሉ። የመልሶ ማቋቋሚያ ኤጀንሲዎ ለጤና አጠባበቅ ክፍያ እንዲከፍሉ እና በዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያ ጊዜ የጤና እንክብካቤ ቀጠሮዎን በሚያመቻቹ ወረቀቶችዎ ዙሪያ ያግዛል። እባክዎን ሁሉንም የህክምና እና የክትባት መዝገቦች ወደዚህ ቀጠሮ ይዘው ይምጡ።
ፋርማሲዎች፣ የዶክተር ቢሮዎች ወይም ክሊኒኮች፣ እና ሆስፒታሎች ሁሉም የጤና እንክብካቤ የሚያገኙባቸው ቦታዎች ናቸው። ችግርዎ ቀላል ወይም መደበኛ ከሆነ፣ በቤት ውስጥ ለማከም የሚያስፈልጎትን መድሃኒት ለማግኘት ወደ ፋርማሲ ይሂዱ። ችግርዎን ለፋርማሲው ሰራተኞች ማስረዳት ይችላሉ እነሱም ትክክለኛውን ህክምና ለመምረጥ ይረዱዎታል። ሁኔታዎን በቤት ውስጥ ማከም ካልቻሉ ወደ ሐኪም ቢሮ ወይም ክሊኒክ ይሂዱ። እንዲሁም ድንገተኛ የሕክምና አደጋ ካጋጠምዎ ወደ 9-1-,1 ይደውሉ ወይም ወደ አስቸኳይ እንክብካቤ ማእከል ወይም የሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ።
አንዳንድ መድሃኒቶች የሐኪም ማዘዣ ያስፈልጋቸዋል፣ሌሎች ደግሞ አያስፈልጋቸወም። የሐኪም ማዘዣዎች በፋርማሲ ውስጥ የሚፈልጉትን መድሃኒት መግዛት እንዲችሉ ዶክተሮች ሊሰጡዎት የሚችሏቸው ልዩ ፈቃዶች ናቸው። ብዙ መድሃኒቶች ያለ ማዘዣ ይገኛሉ፣ሌሎች ግን አይገኙም። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚቆዩበት የመጀመሪያው ወር የሚሆኑ በቂ መድኃኒቶች ከሌልዎ፣እባክዎን ለIOM (ወይም ቀድሞውንም ዩ.ኤስ ውስጥ ከሆኑ፣ለመልሶ ማቋቋሚያ ኤጀንሲዎ) ያሳውቁ።
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያለው የጤና እንክብካቤ ውድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የክፍያ አማራጮች አሉ የመንግስት መርሃ ግብሮች ፣ስደተኞች መጀመሪያ እንደደረሱ እና ለመርሃ ግብሩ ብቁ ለሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች የጤና እንክብካቤ ወጪዎችን ይከፍላሉ። ሌሎች ሰዎች የጤና ወጪዎቻቸውን ለመክፈል በግል የጤና መድን ላይ ይተማመናሉ።
የጤና እንክብካቤ በቋንቋዎ የማግኘት መብት አልዎት። የዶክተሮች ቢሮዎች እና ክሊኒኮች ከህክምና ሰራተኞች ጋር እንዲግባቡ የሚረዱ አስተርጓሚዎች አሏቸው። ስለ ህመምዎ ወይም ስለ ህክምናዎ ያልተረዱት ነገር ካለ የህክምና ባለሙያዎችን ጥያቄዎች ይጠይቁ።
የጤና እንክብካቤ ግላዊነቱ የተጠበቀ ነው። ሐኪምዎ፣ ክሊኒክዎ ወይም ፋርማሲዎ ስለ ጤና አንክብካቤዎ መረጃ ያለ እርስዎ ፈቃድ ለማንም - ለቤተሰብዎም ቢሆን ማጋራት አይችልም።